እሑድ 23 ማርች 2014

                                                   የዐቢይ ጾም 5ኛ ሳምንት

       የዐቢይ ጾም 5ኛ ሳምንት
              ደብረ ዘይት- የምጽአት መታሰቢያ
        ደበረ ዘይት

"የሚያስታችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፡፡ ብዙዎች እኔ ክርስቶስ
ኝ     እያሉ በስም ይመጣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ" ማቲ፡24፡5-8
ያብይ ጾም አምስትኛ ሳምንት ደብረዘይት ነው፡፡

ደብረዘይት የጾም እኩልታ ነው ትርጉሙም ደብር ማለት ተራራ ዘይት ደግሞ የወይራ ዘይት የሞላበት ቦታ ነው:: ቦታው ከምስራቅ እየሩሳልም ከጎሎጎታ ተራራ በግምት ሁለት ኪሎ ሜትር እርቀት አለው ::

በዚህም ቦታ መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዘመነ ስጋዊ ጉዞ በደብረ ዘይት ተራራ ያልፍ እንደነበርና እንዳስተማረ መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል ማቴ-24:1-36
 
                                                        

በዚህም ተራራ ስለ አለም ምጽአት ስለዳግም መምጣቱም አስተምሮአል ክርስቶስ ስለዳግም ምጽአቱ ባስተማረ ጊዜ
ለደቀ መዛሙርቱ
        “ይህን ሁሉ ታያላችሁን ዲንጋይ በዲንጋይ ላይ ሳይፈርስ   በዚህ   አይቀርም'' ማቴ 24፡2-3

አላቸው ደቀ መዛሙረቱም ስለአለም ፈጻሜ ምልክተ ጠየቁት ክርሰቶስም ስለመምጣቱና ምልክቱን ነገራቸው

ዲንጋይ በዲንጋይ ላይ ይፈርሳል
ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ ብለው ይነሳሉ
ጦርነትና የጦርነት ወሬ ይሰማል
ህዝብ በህዝብ ላይ መንግስትም በመንግስት ላይ ይነሳል
በዙዎችም ሀይማኖታቸውን ይለውጣሉ
ቸነፈርና የምድርም መናወጥ ይሆናል

መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዘመነ ስጋዊ ጉዞ በደብረ ዝይት ተራራ ስልአለም ፍጻሜ ያስተማራቸው ትምህርቶች የምጽአቱ ምልክቶች ዲንጋይ በዲንጋይ ላይ ይፈርሳል
ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ ብለው ይነሳሉ
ጦርነትና የጦርነት ወሬ ይሰማል
ህዝብ በህዝብ ላይ መንግስትም በመንግስት ላይ ይነሳል
በዙዎችም ሀይማኖታቸውን ይለውጣሉ
ቸነፈርና የምድርም መናወጥ ይሆናል

ዛሬ በዘመናችን እየተነሱ ናቸው ::
ብዙዎችም ሃይማኖታቸውን ከመለወጣቸው የተነሳ ዛሬ ለቁጥር የሚያስቸግሩ ሃይማኖቶች በምድራችን ላይ ይገኛሉ መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላል

''ከነዚህ ቀኖች መከራ በኋላ ወዲያውኑ ጸሀይ ይጨልማል ጨረቃም ብርሃኑን አይሰጥም ክዋክብቱም ከሰማይ ይወድቃሉ የሰማያት ኃይልም ይናወጣል'' ማቴ 24፡29-30



የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ

እንዘ ይነብር እግዚእነ ውስተ ደብረ ዘይት ወይቤሎሙ ለአርዳኢሁ ዑቁኬ ኢያስሕቱክሙ ወንበሩ ድልዋኒክሙ ብዙኃን ይመጽኡ በስምየ እንዘ ይብሉ አነ ውእቱ ክርስቶስ ወዘአዝለፈ ትዕግሥቶ ውእቱ ይድኅን ወአመ ምጽአቱሰ ለወልደ እጓለ እመሕያው ይትከወስ ኲሉ ኃይለ ሰማያት ወምድር አሜሃ ይበክዩ ኲሎሙ ኃጥአነ ምድር፡፡ ወይወርድ እግዚእነ እምሰማይ ዲበ ምድር በትእዛዙ ወበቃሉ ወበ አዕላፍ መላእክቲሁ በንፍሐተ ቀርን ዘእም ኀበ እግዚአብሔር ይምሐረነ አብ በይእቲ ሰዓት እሞተ ኃጢአት እስመ ገባሬ ሕይወት ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት፡፡

ትርጉም:- ጌታችን በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ ለደቀ መዛሙርቱ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፤ተዘጋጅታችሁም ኑሩ፤ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ እስከ መጨረሻው የጸና እርሱ ይድናል፡፡ የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜ የሰማያትና የምድር ኃይላት ሁሉ ይናወጣሉ።ያን ጊዜ በምድር ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ ያለቅሳሉ አላቸው፡፡ጌታችንም ከባሕርይ አባቱ ከእግዚአብሔር አብ ዘንድ በመለከት ድምፅ ከአእላፍ መላእክት ጋር በግርማ መለኮቱ ከሰማይ ወደ ምድር ይወርደል፡፡ በዚች ዕለትም ከሞተ ኃጢአት አብ ይማረን የሕይወት ባለቤት የሰንበትም ጌታ ነውና፡፡

ምንባባት መልዕክታት
(1ኛተሰ.4÷13-ፍጻ.) ወንድሞቻችን ሆይ÷ ስለ ሞቱ ሰዎች÷ ተስፋ እንደሌላቸው ሰዎች እንዳታዝኑ ልታውቁ እንወዳለን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞቶ እንደ ተነሣ ካመንን እንዲሁ እግዚአብሔር ሙታንን በኢየሱስ ያስነሣቸዋል፤ ከእርሱም ጋር ያመጣቸዋል፡፡ .......
(2ኛ ጴጥ.3÷7-14) አሁንም ሰማይና ምድር በዚያ ቃል ለእሳት ተዘጋጅተዋል፤ ኃጥኣን ሰዎች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀንም ተጠብቀዋል፡፡ነገር ግን ወንድሞቻችን ሆይ÷ ይህን አትርሱ፤ በእግዚአብሔር ዘንድ አንዲት ቀን እንደ አንድ ሺህ ዓመት÷ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን ነውና፡፡

ግብረ ሐዋርያት
(የሐዋ. 24÷1-21) በአምስተኛውም ቀን ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ከመምህራኑና ጠርጠሉስ ከሚባል አንድ ጠበቃ ጋር ወረደ፤ ጳውሎስንም በአገረ ገዢው ዘንድ ከሰሱት፡፡ ጳውሎስም በቀረበ ጊዜ ጠርጠሉስ እንዲህ እያለ ይከስሰው ጀመረ፤ “ክቡር ፊልክስ ሆይ÷ በዘመንህ ብዙ ሰላምን አግኝተናል፤ በጥበብህም በየጊዜው በየሀገሩ የሕዝቡ ኑሮ የተሻሻለ ሆኖአል፤ ሥርዐትህንም በሁሉ ዘንድ ስተመሰገን አግኝተናታል፡፡(ተጨማሪ ያንብቡ)

ምስባክ
መዝ. 49÷2 እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ፡፡ ወአምላክነሂ ኢያረምም፡፡ እሳት ይነድድ ቅድሜሁ፡፡

ትርጉም፦ እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል፡፡ አምላካችንም ዝም እይልም፤ እሳት በፊቱ ይነድዳል በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ አለ፡፡

ወንጌል
(ማቴ. 24÷1-25)

ቅዳሴ: - ቅዳሴ ዘአትናቴዎስ



      ''ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠንቀቁ አትደንግጡ ነገር  ግን ፍጻሜው    ግና ነው''
ማቴ 24፡6-7